ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ወረዳ 08 ብልጽግና ፓርቲ
ወቅታዊ መረጃዎች
1446ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ የኮርደር ልማት ስራ ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች ጋር በዓልን በስራ ቦታ አክብረናል።
በዓልን ጭምር እየሰሩ የሚያከብሩትን እና የእረፍት ቀናቸውን ሳያርፉ ሀገር ለመገንባት እና ከደህነት ለመዉጣት የሚተጉትን ሁሉ በራሴ እና በከተማዉ አስተዳደር ስም አመሰግናለሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆን በድጋሚ እመኛለሁ።
ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለአቅመ ደካሞችና አረጋውያን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ አስተዳደር ወረዳ 01 በሚገኘዉ የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል የኢድ አል- ፈጥር በአልን አስመልክቶ ማዕድ ማጋራት ተካሄደ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን መጋቢት 21/2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በሚገኘዉ የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ለአረጋዊያንና ለአቅመ ደካሞች የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 1446 ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ማዕድ አጋርቷል።
ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማዕድ ባጋሩበት ወቅት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላፍ አስተዳደሩ አቅም ለሌላቸው እና በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችን በአልን ሳይጨናነቁ አብሮ የማሳለፍ አብሮነትን የሚያጠናክሩ የሰው ተኮር ተግባራትን በተለያዩ ወቅቶች ማከናወኑን አንስተዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አያይዘውም በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጎ ፍቃድ ማዕድ ማጋራትና የሰው ተኮር ተግባራት ከተጀመረ ጀምሮ በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት የቀየረ በርካታ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል።
ባለፉት የለውጥ አመታት የተከናወኑ የሰው ተኮር ተግባራት ኢትዮጵያዊ አብሮነትን መደጋገፍን የጎለበተበት እንደሆነ ገልፀው የረመዳን ወር ያለው ለሌለው የሚረዳዳበት አብሮነትን የሚያጠናክር እንደሆነ ገልፀዋል።
የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ላይም አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ እና ሌሎች አመራሮች ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 446ኛው ኢድ አል_ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!!
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘመድኩን ግርማ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺ 446ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን። በዓሉ የሰላም፣የጤና የመተሳሰብ እና የአንድነት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።
የኢድ አል ፈጥር በዓል ህዝበ ሙስሊሙ በድምቀት ከሚያከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ ነው። በዓሉ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ዕሴቶቻችንን ከፍ አድርገን የምታሳይበት እንደመሆኑ ወገኖቻችንን የምናስብበት እንደሚሆን አምናለሁ ። በመሆኑም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማገዝና ማዕድ በማጋራት በዓሉን እንዲያሳልፍ አደራ እላለሁ።
በድጋሚ መልካም የኢድ አል ፈጥር በዓል!
ኢድ ሙባረክ!!
ኮልፌ ወረዳ 08 ኮሙኒኬሽን
መጋቢት 20/2017 ዓ.ም
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺ 446 ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!
ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዙልፋ ሸምሱ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
ውድ የወረዳችን እስልምና እምነት ተከታዮች ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁንና የተከበረውን የረመዳን ወር በጾም፣ በዱዓ፣ በመተጋገዝ፣ በመረዳዳትና አርአያነት ባላቸው ሌሎች ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች ያሳለፈ መሆኑ ይታወቃል እንደ ወረዳ አስተዳደርም በዚህ ዓመት ያሳለፍነው የረመዳን ወር አቅመ ደካሞችን ያገዝንበት ፤ እርስ በርስ የተደጋገፍንበት ፣ የተለያዩ እምነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ኅብረ ብሔራዊ አንድነታቸውን ፣ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን በጽናት ያሳዩበት ወር ነበር ይህ አብሮነታችን በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡
በመጨረሻም የዘንድሮውን በአል ስናከብር ልክ እንደ ሁልጊዜው አቅመ ደካሞችን እና የተቸገሩትን በመደገፍ እና ማዕድ በማጋራት አብሮነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት እንዲሆን መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
ኮልፌ ወረዳ 08 ኮሙኒኬሽን
መጋቢት 20/2017ዓ.ም
የወረዳው ጠቅላላ አመራር በሁለተኛው ዙር የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ ተይዘው እየተሰሩ ያሉ እና የፓርቲ ተግባራት ያለበት አፈጻጸም ደረጃ ገመገመ!
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር አጠቃላይ አመራር በሁለተኛ ዙር የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ ተይዘው እየተሰሩ ያሉ የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት ያሉበት የአፈጻጸም ደረጃ ተገምግሟል።
በግምገማው ላይም የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ዙልፋ ሸምሱ የዘጠና ቀናት የንቅናቄ እቅዱን እንዲሁም መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን ለማከናወን በጊዜ የለኝም መንፈስ ርብርብ በማድረግ የላቀ ውጤት ማምጣት እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።
የወረዳው የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘመድኩን ግርማ በበኩላቸው ተግባራትን በቅንጅት አስተሳስሮ በመስራት እና እስካሁን ባሉ የስራ ሂደቶች ያጋጠሙትን ክፍተቶች በፍጥነት በማረም ውጤት ማምጣት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
“ባህሎቻችን የወል ትርክት አምባ” በሚል መሪ ቃል በከተማችን ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚከናወነውን 16ኛ የባህል ፌስቲቫል ሳምንት ዛሬ አስጀምረናል።
ባህሎቻችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው ለሀገር ግንባታ፣ ለህዝቦች መቀራረብ፣ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ለሰላም እና ለወል ትርክት ግንባታ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
መላው የከተማችን ነዋሪዎች የሚያጋምዱን እና ከሌላው የዓለም ክፍል የሚለዩን ባህሎቻችን ሃብቶቻችን መሆናቸውን በመረዳት፣ የተዘጋጀውን የባህል ፌስቲቫል በጊዮን ሆቴል በመገኘት እንድትጎበኙ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በወረዳው አስተዳደር የባለ ጉዳይ ቀንን አስመልክቶ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥላል!
ኮልፌ ወረዳ 08 ኮሙኒኬሽን
የካቲት 21/2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት፣ ምክር ቤት እና ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት በጋራ የአገልግሎት ቀን ምክንያት በማድረግ ምልከታ አድርገዋል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዙልፋ ሸምሱ ከሌሎች የተቋም አመራሮች ጋር በመሆን በወረዳው የሚገኙ ነዋሪዎች የሚያቀርቧቸውን የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በማዳመጥ ምላሾችን ችግሮቹ የሚፈቱበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በየተቋማቱ ያሉ የጽ/ቤት ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገልጋዮቻቸውን በቢሮዎቻቸው በመገኘት እያስተናገዱ ሲሆን ተገልጋዮችም በሚሰጣቸው አገልግሎት እርካታ ማግኘታቸው በምልከታ ወቅት ገልፀዋል።
ክፍለ ከተማና ከተማ አቀፍ ሁለንተናዊ ልማት እንዲሳለጥ የተሳካ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎች ማከናወኑ የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ገለፀ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን የካቲት 21/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ባለፉት 6 ወራት ውጤታማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎችን ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ምርምር ሀይሌ እንደገለፁት ፅ/ቤታቸው መረጃዎችን በስፋትና በጥራት ተደራሽ በማድረግ በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሁለንተናዊ የልማት ተግባራት የጋራ መግባባት እንዲፈጠር እንዲሁም በሀገሩና በከተማው ጉዳይ ንቁ ተሳትፎ ኖሮት የራሱን አስተዋጽኦ ከማበርከት አንፃር የተሳካ የሚዲያና ህዝብ ግኑኙነት ተግባራት መሰራታቸውን አስታውቀዋል።
በበጀት አመቱ 6ወራት ከተከናወኑ ዋና ዋና የሚድያ እና ህዝብ ግንኙነት ስራዎች መካከል በተለያዩ አጀንዳዎች የተለያዩ የህትመት ስራዎች አዘጋጅቶ ማሰራጨት፣ የእቅድ እና ጥቆማ ዜናዎች ማሰራጨት፣ የፎቶ ማንሳትና የቪድዮ ቀረፃ ስራዎች፣ የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት መስጠት ይገኙበታል።
ከዚህ በተጨማሪ በክፍለ ከተማው አስተዳደር የተከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የሚያስቃኙ አጫጭር ፖሮግራሞች፣ የኢዲቲንግ ስራዎች፣ ፓናሎች፣ ሁነቶች፣ኢግዚቢሽኖች እና ሌሎች ስራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ወ/ሮ ምርምር ሀይሌ በገለፃቸው ፅ/ቤቱ የነበሩበትን የግብአትና የሰው ሀይል እጥረት እንዲሻሻል ዘመናዊ መረጃ ማእከል በማደራጀት በሂደቱ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና ችግር ፈቺ ጥናቶችን በመተግበር የተቋሙን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም እስከ ወረዳ ድረስ ወጥነት ባለው መልኩ በማሳደግ ረገድ አመርቂ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ3.1 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዢ ማከናወኑን ገለጸ!
ኮልፌ ወረዳ 08 ኮሙኒኬሽን
የካቲት 20/2017 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ሲያካሄድ የነበረውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሃብት ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት በማጠናቀቅ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር አስረክቧል።
የወረዳው አስተዳደር ለታላቁ የህዳሴ ሀብት ማሰባሰቢያ ዋንጫ ተረክቦ የቦንድ ግዢ ንቅናቄ በማካሔድ ከእቅዱ በላይ ከ3.1 ሚሊየን ብር በላይ ማሰባሰብ ችሏል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዙልፋ ሸምሱ እንደተናገሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለእኛ ኢትዮጲያውያን የወል እውነታ መሆኑን ተናግረው በወረዳው በንቅናቄው ከ3.1 ሚሊየን ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን አስታውቀዋል። ሀላፊዋ አክለውም ህዳሴ ኢትዮጵያውያንን አንድ ላይ ያስተሳሰረ ማህተም ነው ያሉ ሲሆን በዚህ ተግባር ላይ ለተሳተፉ እና አስተዋጽኦ ላበረከቱ የወረዳው ነዋሪዎች እና ተቋማት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የክፍለ ከተማው ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድራህማን ክብረት እንደተናገሩት ህዝባችን እና ሀገራችን እንደ ታላቀ ህዝብና እንደ ታላቅ ሀገር የከወናቸው፣ ያደረግናቸው ወጥንን ያሳካናቸው፣ አስበን የፈጸምናቸው እና ጀምረን የጨረስናቸው የበርካታ ገድሎች እንዳሉን ያነሱ ሲሆን የታላቁ ህዳሴ ግድብን የእኛ የኢትዮጲያውያን የወል እውነታ በመሆኑ እንደጀመርን በአንድነት እና በህብረት እንጨርሰዋለን ብለዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቃሲም ሱሩር ዋንጫውን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ታላቁ የህዳሴ ግድብ በራስ አቅም እየገነባነው ያለ ታላቅ ታሪክ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ በወረዳቸው በሚካሔደው የቦንድ ግዢ ንቅናቄ ላይ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም የወረዳ 08 አስተዳደር የሃብት ማሰባሰቢያ ዋንጫውን ለወረዳ 10 አስረክቧል።
#ታላቁ_የህዳሴ_ግድብ_የኢትዮጲያውያን_የወል_እውነታ!
Heads of Government Ethiopia
Abiy Ahmed Ali : Abiyi Ahmed Alii; Amharic: ዐቢይ አሕመድ ዐሊ; born 15 August 1976) is an Ethiopian politician serving as the third Prime Minister of Ethiopia since 2018, and as the leader of the Prosperity Party since 2019.[1][2] He was awarded the 2019 Nobel Peace Prize “for his efforts to achieve peace and international cooperation, and in particular for his decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea“..
The president of Ethiopia is the head of state of Ethiopia. The position is largely ceremonial with executive power vested in the Council of Ministers chaired by the prime minister. The current president Taye Atske Selassie Amde (Amharic: ታዬ አጽቀሥላሴ, born 13 January 1956) is an Ethiopian diplomat and politician who is serving as president of Ethiopia since 7 October 2024. He has worked as ambassador on numerous occasions in the United Nations. Prior to assuming this role, he served as the Minister of Foreign Affairs.
Adanech Abebe : Adaanach Abeebee) is an Ethiopian politician and attorney who is serving as the thirty-second mayor of Addis Ababa since 2021. She has been serving as a deputy mayor from 2020 until 2021. She previously was the Minister of Revenue and Customs Authority from 2018[1][2] to 2020, when she became the first female to assume the role of the Federal Attorney General of Ethiopia.[3][4][5][6] She is the first woman to hold the mayorship since it was created in 1910.[